Kahn

2 views

Lyrics

በቃላት ድርድር በሙዚቃ ቃና
 ስሜን ስታብራራ ነፍሴን ስታጣራ
 አየሁኝ ጥበብ ሰማሁኝ ዕውቀት
 ልናገር ልመስክር የዚህን ሰው ጽናት
 ቀልጦ እንደሚበራ ሻማ
 መብራት በሌለው ከተማ
 እየቀለጠ በራልኝ
 እየሞተ አኖረኝ
 ለሱስ ባለእዳው ነኝ
 ህይወት እንዳይሰለቸኝ
 ሲጨነቅ ሲጠበብ
 አይተኛም ቀን ከሌት
 ለደስታዬ ሲዋትት
 ካህንዬ የነፍሴ አገልጋይ
 እንቅልፍ አትተኛም ወይ
 የነፍሴ አገልጋይ
 እንቅልፍ አትተኛም ወይ
 ካህንዬ የነብሴ አገልጋይ
 እንቅልፍ አትተኛም ወይ
 የነፍሴ አገልጋይ
 እንቅልፍ አትተኛም ወይ
 መሰንቆዉን ይዞ ከደጄ
 ሲጫወት ያድራል ሲያዜም
 በበገና በክራር ነፍሴን ሲያለመልም
 እንደ መልከጼዴቅ ካህን
 ክህነቱ ከዘመን ዘመን
 የዘላለም አይደለም ወይ
 የሰጠኝ ደስታ ከላይ
 ስወድ ስጠላ የማይተወኝ
 ለትንሽ ደስታው አመስጋኝ
 አንዲህ ያለ ሰው የሰው ምርጥ
 በጊዜ የማይለወጥ
 ካህንዬ የነፍሴ አገልጋይ
 እንቅልፍ አትተኛም ወይ
 የነፍሴ አገልጋይ
 እንቅልፍ አትተኛም ወይ
 ቃል ከአንደበቱ እንደውሃ
 ይፈሳል እንደ ጅረት
 ልብን የሚመረምር
 ጠልቆ የሚገባ ከአንጀት
 ሰምና ወርቁን ተናገር
 ቅኔ በለሱን ደርድር
 በጻድቅ ሰው ቃላት
 ነፍሴ ገባች ከገነት
 ጣዕሙን ዜማ ስታዜም
 ቃልን ከህይወት ስትቀምም
 ስጋዬን ለየህ ከነፍሴ
 አቆራረጥከኝ ከእስትንፋሴ
 ካህንዬ የነፍሴ አገልጋይ
 እንቅልፍ አትተኛም ወይ
 የነፍሴ አገልጋይ
 እንቅልፍ አትተኛም ወይ
 እንደ መልከጼዴቅ ካህን
 ክህነቱ ከዘመን ዘመን
 የዘላለም አይደለም ወይ
 የሰጠኝ ደስታ ከላይ
 ከላይ ከላይ
 ከላይ ከሰማይ
 ከላይ ከላይ
 ከላይ ከሰማይ
 ከሰማይ
 

Audio Features

Song Details

Duration
03:47
Key
5
Tempo
92 BPM

Share

More Songs by Gigi

Albums by Gigi

Similar Songs