Abet Wubet

7 views

Lyrics

ሸማ ነጠላውን ለብሰው
 ሸማ ነጠላውን ለብሰው
 አይበርዳቸው አይሞቃቸው
 ሀገሩ ወይናደጋ ነው
 አቤት ደምግባት ቁንጅና
 አፈጣጠር ውብ እናት
 ሀገሬ እምዬ ኢትዮጵያ
 ቀጭን ፈታይ እመቤት
 በእምዬ ማርያም በአዛኝቱ
 ኑሪልኝ እናት ዓለሚቱ
 በእምዬ ማርያም በአዛኝቱ
 ኑሪልኝ እናት ዓለሚቱ
 ልብስህን የሀገሬ ሰው
 ጃኖህን የሀገሬ ሰው
 ልብስህን የሀገሬ ሰው
 ያምራል ኮርተህ ልበሰው
 በራያ ቀሚስ በጃኖሽ
 በቀጭን ኩታ በሻሽሽ
 በድሪ አምባርሽ በእግርሽ አልቦ
 ይታይ ሰውነትሽ ተውቦ
 አቤት አቤት አቤት አቤት
 ሸማ ነጠላውን ለብሰው
 ሸማ ነጠላውን ለብሰው
 አይበርዳቸው አይሞቃቸው
 ሀገሩ ወይናደጋ ነው
 አቤት ደምግባት ቁንጅና
 አፈጣጠር ውብ እናት
 ሀገሬ እምዬ ኢትዮጵያ
 ቀጭን ፈታይ እመቤት
 በእምዬ ማርያም በአዛኝቱ
 ኑሪልኝ እናት ዓለሚቱ
 በእምዬ ማርያም በአዛኝቱ
 ኑሪልኝ እናት ዓለሚቱ
 ልብስህን የሀገሪ ሰው
 ኩታህን የሀገሪ ሰው
 ጃኖህን የሀገሪ ሰው
 ያምራል ኮርተህ ልበሰው
 ሸጌው ኩታህን ልበስና
 በቀዩ ጃኖ ተውበህ ና
 አውዳመት ይሁን ከተማው
 ነጭ በነጩን ልበሰው
 አቤት አቤት አቤት አቤት አቤት
 አቤት ውበት አቤት ውበቷ
 እዩልኝ ወርቁን ከአንገቷ
 ያብረቀርቃል ደረቷ
 እጇ ላይ ያለው ብር አምባር
 እዩልኝማ ሲያምር
 አቤት አቤት አቤት አቤት
 አቤት አቤት አቤት አቤት
 አቤት ውበት አቤት
 አቤት ውበት አቤት
 አቤት አቤት አቤት አቤት አቤት አቤት አቤት
 አቤት ውበት አቤት ውበቱ
 ወርቁ ተጥሎበት ካንገቱ
 ያበረቀርቃል ደረቱ
 ከጆሮው ያንጠለጠለው
 ሎቲውን ባረገኝ ምነው
 አቤት አቤት አቤት አቤት
 ውበት ውበት ውበት ውበት ውበት ውበት

Audio Features

Song Details

Duration
06:39
Key
3
Tempo
89 BPM

Share

More Songs by Gigi

Albums by Gigi

Similar Songs