Guramayle

9 views

Lyrics

ዓይኑ ማረከኝ ስል ከንፈሩ ገሎኛል
 ደሞ ከሞትኩበት ፍቅር ያስነሳኛል
 Dear my love ይለኛል ከዚያም የኔ ፍቅር
 ስንቱን ቋንቋ ችዬ ከሱ ልነጋገር
 ጉራማይሌ ልጁ ጉራማይሌ ቋንቋው
 ጉራማይሌ ልጁ ጉራማይሌ ቋንቋው
 ጉንፌን አውልቄ ለበስኩኝ ቦላሌ
 ጉራማይሌ ልጁ ጉራማይሌ ቋንቋው
 ጉራማይሌ ልጁ ጉራማይሌ ቋንቋው
 ጉንፌን አውልቄ ለበስኩኝ ቦላሌ
 ♪
 የተቀባው ሽቶ የገላው ጠረን
 ብሉኝ ብሉኝ ይላል የቀረቡት እንደሆን
 ከከንፈር ከጥርሱ ከአይኑ ፍቅር ይዞኝ
 እወዘወዛለሁ ኸረ ማን ያስጠለኝ
 ጉራማይሌ ልጁ ጉራማይሌ ቋንቋው
 ጉራማይሌ ልጁ ጉራማይሌ ቋንቋው
 እመቤቴ ማርያም አርጊልኝ የግሌ
 ጉራማይሌ ልጁ ጉራማይሌ ቋንቋው
 ጉራማይሌ ልጁ ጉራማይሌ ቋንቋው
 ጉንፌን አውልቄ ለበስኩኝ ቦላሌ
 ♪
 አካል ሰውነቱ እንደ ህፃን ልጅ
 አቤት መለስለሱ አቤት ሲያስጎመጅ
 የኔ እግር እንዳንተ ምን አለሰለሰው
 ከኔ ቤት አንተ ቤተ የተመላለሰው
 ጉራማይሌ ልጁ ጉራማይሌ ቋንቋው
 ጉራማይሌ ልጁ ጉራማይሌ ቋንቋው
 ጉንፌን አውልቄ ለበስኩኝ ቦላሌ
 ጉራማይሌ ልጁ ጉራማይሌ ቋንቋው
 ጉራማይሌ ልብሱ ጉራማይሌ ቋንቋው
 እመቤቴ ማርያም አርጊልኝ የግሌ
 ♪
 በፈረንሳዮቹ ቋንቋ በእንግሊዘኛ ቢናገር
 በጣልያንኛ ቢገጥም በጀርመንኛ ቢፎክር
 ከአፉ ማር ይፈሳል ልጁ ለዛ አለው አንደበቱ
 እስቲ ይጫወት ይፈንድቅ ያለሱ አይደምቅም ቤቱ
 ጨዋታህ ይናፍቀኛል ያራዳ ልጅ ቆንጆ ሰው
 በለሰለሱ እጆችህ ና ገላዬን ደባብሰው
 ♪
 ጉራማይሌ
 ጉራማይሌ
 ጉራማይሌ
 ጉራማይሌ
 ጉራማይሌ
 ጉራማይሌ
 ጉራማይሌ
 ጉራማይሌ
 

Audio Features

Song Details

Duration
04:27
Key
2
Tempo
94 BPM

Share

More Songs by Gigi

Albums by Gigi

Similar Songs