Tew Ante Sew

5 views

Lyrics

አሞራ ወድጄ አሞራ ሆኛለው
 ነብርን ወደጄ ነብር ሆኜ አውቃለው
 ድብ አንበሳም ነበርኩ ከጥንት ተዋድጄ
 ዛሬ ግን አቃተኝ ብርቄን ሰው ወድጄ
 ሰው መሆን አልቻልኩም ብርቄን ሰው ወድጄ
 ተው አንተ ሰው
 ልቤን አደከምከው
 ተው አንተ ሰው
 ልቤን አደከምከው
 ዘንድሮ ይህ መውደድ የጣለብኝ እዳ
 ሰው እንዴት ይወዳል ሰውን ሳይረዳ
 ፍቅር አጠናገረኝ እንደ ጠጠር ምች
 መድሃኒት ፈልጉ 'ምታውቁ ሰዎች
 ተው(ተው) አንተ ሰው
 አሞራ ወድጄ አሞራ ሆኛለው
 ነብርን ወድጄ ነብር ሆኜ አውቃለው
 ድብ አንበሳም ነበርኩ ከጥንት ተዋድጄ
 ዛሬ ግን አቃተኝ ብርቄን ሰው ወድጄ
 ሰው መሆን አልቻልኩም ብርቄን ሰው ወድጄ
 ተው አንተ ሰው
 ልቤን አደከምከው
 ተው አንተ ሰው
 ልቤን አደከምከው
 እኔም ግራ ገብቶኝ ግራ አጋባው ሰው
 ፍታኝ ከዚህ ማሰር ፍታኝ አንተ ሰው
 እንዲህ ከሆነማ የፍቅር ነገር
 ከሃውልት ከድንጋይ ከእንጨት ልቆጠር
 ተው(ተው) አንተ ሰው
 ተው(ተው) አንተ ሰው
 ንገረኝ አንተ ልጅ ዝም አትበለኝ ምነው
 ጉንፋን እኮ አይደለም የያዘኝ ፍቅር ነው
 ቀልቤ ተበታትኖ ማሰብ ተስኖኛል
 ሰው አርገኝ አንተ ሰው
 ሰው መሆን አቅቶኛል
 ተው(ተው) አንተ ሰው
 ተው ተው ተው
 አንተ ሰው

Audio Features

Song Details

Duration
04:20
Key
8
Tempo
93 BPM

Share

More Songs by Gigi

Albums by Gigi

Similar Songs