Fanno

1 views

Lyrics

ፋኖ ፋኖ
 ኧረ ፋኖ ፋኖ
 ኧረ ፋኖ ፋኖ
 ተኩሶ ሲነጉድ የፈሪ ልምደኛ
 ፊለፊት ተጋዳይ ፋኖ እንደ መጋኛ
 ኧረ ተው በሉት ያንን ባለ ቡሎ
 ሰጠው ለነፋስ አንጓሎ አንጓሎ
 አንጓሎ አንጓሎ
 እንደ ቆላ ወፍ እንደ ግሪሳ
 እንደ ቆላ ወፍ እንደ ግሪሳ
 ያረፍው ልቤ ደግሞ ተነሳ
 ደግሞ ተነሳ
 ፋኖ ፋኖ
 ፋኖ ፋኖ
 ግራር ተልጦ ደግሞ አይላጥም
 ቁርጥ አልሽልኝ እንደ ውሃ ጥም
 እንደ ውሃ ጥም
 ፋኖ ፋኖ
 ሐረር ለኦጋዴን ምን ያህል ይርቃል
 ትዝ ባልሽኝ ግዜ እንባዬ ይመጣል
 እልም ያለው ጫካ እልም ያለው ዱር
 ሲነጋገር ያድራል ከመውዜሩ ጋር
 ከመውዜሩ ጋር
 እንኳን ባልእንጀራ ልብ አይታመን
 ፋኖ ፋኖ
 ፋኖ ፋኖ
 ኧረ ፋኖ ፋኖ
 ፋኖ ሀገሩ ገባ ሳይሰናበተኝ
 ያ ጀግናው ወታደር ሰውም አያደርገኝ
 ሰውም አያደርገኝ
 ፋኖ ፋኖ
 ፋኖ ፋኖ
 እበላው በርጨቃ ልኳንዳው ምን ሆኖ
 የልቤ አስታማሚ ና ፋኖ ና ፋኖ
 ና ፋኖ ና ፋኖ
 ኦሆሆ
 ተው ሳበው ሳበው
 ሳበው መሸብህ
 ሳበው መሸብህ
 የጆቢራ እራት ግብር አለብህ
 ግብር አለብህ
 ግብር አለብህ
 ፋኖ ፋኖ
 የወንድ ልጅ እናት ታጠቂ በገመድ
 የወንድ ልጅ እናት ታጠቂ በገመድ
 ልጅሽን አሞራ እንጅ አይቀብረውም ዘመድ
 አይቀብረውም ዘመድ
 ፋኖ ፋኖ
 ፋኖ ፋኖ
 ከባልእንጀራው ማታ የተለየ
 ከባልእንጀራው ማታ የተለየ
 እንደ አጥቢያ ኮኮብ ሲነጋ ታየ
 ሲነጋ ታየ
 ፋኖ ፋኖ
 ኧረ ተው በሉት
 ኧረ ተው በሉት ያንን ባለ ቡሎ
 ሰጠው ለነፋስ አንጓሎ አንጓሎ
 አንጓሎ አንጓሎ
 ፋኖ ፋኖ
 ፋኖ ፋኖ አለችው ፍንን ያድርጋትና
 ፍንን ያድርጋትና
 ግንድ አልብሶ መጣ ማለቷ ቀረና
 ማለቷ ቀረና
 ፋኖ ፋኖ
 ፋኖ ፋኖ
 የምር ተኳሹን እኛ ስናውቀው
 ዝናር በእቅፌን ማን ደባለቀው
 ማን ደባለቀው
 ፋኖ ፋኖ
 ፋኖ ፋኖ
 ፋኖ ፋኖ
 ወዘት በይ ልቤ እንደ ጀበና
 እንደ ጀበና
 አልወጣልሽም የጦር ባፈና
 የጦር ባፈና
 የጦር ባፈና
 የጦር ባፈና
 የጦር ባፈና

Audio Features

Song Details

Duration
05:36
Key
7
Tempo
125 BPM

Share

More Songs by Kassa Tessema

Similar Songs