Tezeta

3 views

Lyrics

ትናንትናን ጥሶ ዛሬን ተንተርሶ
 ነገንም ተውሶ አምናንም አፍርሶ
 ይመጣል ትዝታሽ ጏዙን አግበስብሶ
 ይመጣል ትዝታሽ ጏዙን አግበስብሶ
 ፍቅርንስ ሸኘሁት ወጥቼ እስከ ደጅ
 መውደድን ሸኘሁት ወጥቼ እስከ ደጅ
 ማባረር ያቃተኝ ትዝታን ነው እንጅ
 ማባረር ያቃተኝ ትዝታን ነው እንጅ
 ጎን ለጎን ሲሆን ፍቅር ነው ደስታ
 አበሳ አስቆጣሪው የተለዩ ለታ
 አልገባኝም እኔ ምንድን ነው ትዝታ
 አልገባኝም እኔ ምንድን ነው ትዝታ
 ትዝታ ነው አሉን የሀሳብ መርከቡ
 ትዝታ ነው አሉን የጭንቀት መርከቡ
 ማራገፊያውማ እኔ ነኝ ወደቡ
 ማራገፊያውማ እኔ ነኝ ወደቡ
 ምንኛ ባጠረ እድሜው የፍቅር
 መዝገበ ቃላቱ ትዝታ ባይኖር
 የትዝታን ዳገት ወጣሁት ተክዤ
 የትዝታን ዳገት ወጣሁት ተክዤ
 በእጄ ምናምኑን በልቤ አንቺን ይዤ
 በእጄ ምናምኑን በልቤ አንቺን ይዤ
 የምትራመዱ እንደተመቻችሁ
 አጅሬ ትዝታ ያልደረሰባችሁ
 እስኪ አውሱኝ ለኔ ደህና ልብ ያላችሁ
 እስኪ አውሱኝ ለኔ ደህና ልብ ያላችሁ
 በልቼ እርቦኛል ጠጥቼ ጠምቶኛል
 ሌሊት እየመጣ እንቅልፍ ይነሳኛል
 ጠላቴ ትዝታን ማን ሰው ያስጥለኛል
 ጠላቴ ትዝታን ማን ሰው ያስጥለኛል
 ኦሆሆሆሆ ኦሆሆሆሆ
 ኦሆሆሆሆ ኦሆሆሆሆ
 ኦሆሆሆሆ ኦሆሆሆሆ
 ኦሆሆሆሆ ኦሆሆሆሆ
 

Audio Features

Song Details

Duration
05:45
Key
5
Tempo
157 BPM

Share

More Songs by Mahmoud Ahmed

Similar Songs