Musherayie

1 views

Lyrics

የልብሽ ቀለሙ ከልቤ ሰመረ
 አንድ ደም ረጨ አንድ ቃል ዘመረ
 ባንድ ተዋደዱ ምታቸው ገጠመ
 የዘላለም ቤቴ ዛሬ ባንቺ ቆመ
 እንኳን በህይወትሽ እንኳን በህይወቴ
 በአዳም ልጆች እዳ በሞትሽ በሞቴ
 አልወጣም ከቃልሽ ከእምነትሽ ከእምነቴ
 ከዘላለም ቤትሽ ከዘላለም ቤቴ
 ሙሽራዬ ሙሽራዬ
 የወይን አበባዬ
 ሙሽራዬ ሙሽራዬ
 የወይን አበባዬ
 የማንነቴ ልክ መለኪያ ሚዛኔ
 የኑሮዬ ትርጉም የህይወት ወሰኔ
 የመንገዴ ማሾ የእድሜ ብርሃኔ
 የዘላለሜ ነሽ የነብስ ኪዳኔ
 እንኳን በህይወትሽ እንኳን በህይወቴ
 በአዳም ልጆች እዳ በሞትሽ በሞቴ
 አልወጣም ከቃልሽ ከእምነትሽ ከእምነቴ
 ከዘላለም ቤትሽ ከዘላለም ቤቴ
 ሙሽራዬ ሙሽራዬ
 የወይን አበባዬ
 ሙሽራዬ ሙሽራዬ
 የወይን አበባዬ
 

Audio Features

Song Details

Duration
04:21
Key
4
Tempo
157 BPM

Share

More Songs by Michael Belayneh

Similar Songs