Why

2 views

Lyrics

ሰኞ ደህና ውዬ
 ማክሰኞ ያመኛል
 እሮብ ደህና ሳ'ድር
 ሐሙስ ያቃዠኛል
 አርብ እንደዚያው ነበር
 ቅዳሜም እንዲያው ነው
 እሁድ ደህና ውዬ
 ሰኞ መታመም ነው
 አንድ ቀን ሲጨልም
 አንድ ቀን ብርሃን ነው
 አንዱ ቀን ሲበርደኝ
 አንዱ ቀን ሞቃት ነው
 ፍቅር እንዲህ ነው ወይ
 እኔ ምን አውቃለሁ
 አንድ ቀን ደስ ሲለኝ
 አንድ ቀን አዝናለሁ
 ሁሌም እንዲህ ነበር
 ሁሌም እንደዚህ ነው
 ዛሬ እንዳላወቀ መገረሜ ምነው
 ኧረ ምነው ኧረ ምነው
 ኧረ ምነው ኧረ ምነው
 ኧረ ምነው ኧረ ምነው
 ሁሌም እንዲህ ነበር
 ሁሌም እንደዚህ ነው
 አምና ሲያመኝ ኖሮ
 ዘንድሮ ጠናብኝ
 ያቻምና ህመሜ
 ይዞ አለቅም አለኝ
 እኔ ምን አውቃለሁ
 ዘንድሮም እንዲያው ነኝ
 አቻ'ምና እና አምና
 ተፈራረቀብኝ
 እባክህ አምላኬ
 የምለምንህ
 ካ'ምናው በሽታዬ
 አውጣኝ እባክህ
 ሁሌም እንዲህ ነበር
 ሁሌም እንደዚህ ነው
 ዛሬ እንዳላወቀ መገረሜ ምነው
 ኧረ ምነው ኧረ ምነው
 ኧረ ምነው ኧረ ምነው
 ኧረ ምነው ኧረ ምነው
 ሁሌም እንዲህ ነበር
 ሁሌም እንደዚህ ነው
 እንዲያ እንዲያ እያለ
 ግዜው ይረዝምና
 እንራራቃለን
 ቀርቶብን ዝምድና
 በሽታዬ ፀንቶ
 ሞት ይወስደኝና
 ያስተዛዝበናል
 ይሄ ቀን ያልፍና
 እባክሽ አንቺ ቀን
 ቶሎ ቶሎ እለፊ
 ያገኘ ሰው ሲያጣ
 ይመስላል ቀጣፊ
 ሁሌም እንዲህ ነበር
 ሁሌም እንደዚህ ነው
 ዛሬ እንዳላወቀ መገረሜ ምነው
 ኧረ ምነው ኧረ ምነው
 ኧረ ምነው ኧረ ምነው
 ኧረ ምነው ኧረ ምነው
 ሁሌም እንዲህ ነበር
 ሁሌም እንደዚህ ነው
 አንዱ ትዳር ይዞ
 አንዱ ብቸኛ ነው
 አንዱ ለቅሶ ሲሄድ
 አንዱ ራቆቱን ነው
 አንዱ ጠግቦ ሲያድር
 አንዱ ረሀብተኛ ነው
 አንዱ ቤት ሲኖረው
 አንዱ ሀገርም የለው
 አንዱ ባ'ገር ሲኖር
 አንዱ በስደት ነው
 አንዱ ደፋር ሲሆን
 አንደኛው ፈሪ ነው
 ሁሌም እንዲህ ነበር
 ሁሌም እንደዚህ ነው
 ዛሬ እንዳላወቀ መገረሜ ምነው
 ኧረ ምነው ኧረ ምነው
 ኧረ ምነው ኧረ ምነው
 ኧረ ምነው ኧረ ምነው
 ዛሬም እንዲህ ነበር
 ዘንድሮም እንዲያው ነው
 ሁሌም እንዲህ ነበር
 ሁሌም እንደዚያው ነው
 

Audio Features

Song Details

Duration
06:41
Key
5
Tempo
176 BPM

Share

More Songs by Teshome Mitiku

Albums by Teshome Mitiku

Similar Songs