Ateshguwatem Woy

3 views

Lyrics

አትሸኛትም ወይ አሀሀ
 አትሸኗትም ወይ መሄዷ አይደለም ወይ
 አትሸኙትም ወይ ኦሆሆ አትሸኑትም ወይ ሊሄድ አይደለም ወይ
 አትሸኙትም ወይ ኦUU አትሸኑትም ወይ ሊሄድ አይደለም ወይ
 አትሸኟትም ወይ አሀሀ
 አትሸኟትም ወይ መሄዷ አይደለም ወይ
 ሊሄድ አይደለም ወይ
 ሊሄዱ አይደለም ወይ
 አትሸኙትም ወይ ኦUU
 አትሸኑትም ወይ ሊሄድ አይደለም ወይ
 በሉ እንሸኛቸዉ በሉ እንሸኛቸዉ ጐጆ ወጪ ናቸዉ
 በሉ እንሸኛቸዉ አሀሀ በሉ እንሸኛቸዉ ጐጆ ወጪ ናቸዉ
 አዲስ ቤተ ሰሪ ጎጆ ወጪ ናቸዉ
 በሉ እንሸኛቸዉ በሉ እንሸኛቸዉ ጐጆ ወጪ ናቸዉ
 እንመርቃቸዉ እንመርቃቸው ብለን ያዝልቃቸዉ
 እንመርቃቸዉ እንመርቃቸው ብለን ያዝልቃቸዉ
 በአዲሱ ቤት በአዲሱ ቤ ት ልጅ ይፈንጭበት
 በአዲሱ ቤት በአዲሱ ቤት ልጅ ይፈንጭበት
 የዛሬ አመት የዛሬ አመት ሁኝ የልጅ እናት
 የዛሬ አመት አሀሀ የዛሬ አመት ሁኝ የልጅ እናት
 የዛሬ አመት ኦሆሆ የዛሬ አመት ሁን የልጅ አባት
 የዛሬ አመት አሀሀ የዛሬ አመት ሁን የልጅ አባት
 ለክርስትና ኦሆሆ ለልደት ደግሞ ያድርሰን ለከርሞ
 ለክርስትና ኦUU ለልደት ደግሞ ያድርሰን ለከርሞ
 አለ ገና አለ ገና አለ ገና ገና አለ ገና
 የሚዜዋም አለ ገና (አለ ገና ገና አለ ገና)
 የሚዜዉም አለ ገና (አለ ገና ገና አለ ገና)
 የእህቶቿም አለ ገና (አለ ገና ገና አለ ገና)
 የወንድሟም አለ ገና (አለ ገና ገና አለ ገና)
 የእህቶቹም አለ ገና (አለ ገና ገና አለ ገና)
 የወንድሙም አለ ገና (አለ ገና ገና አለ ገና)
 የአጃቢዉም አለ ገና (አለ ገና ገና አለ ገና)
 የአጃቢዋም አለ ገና (አለ ገና ገና አለ ገና)
 አለ ገና አለ ገና አለ ገና ገና አለ ገና
 ከእንግዲህ ብቸኝነት ቀረ
 የሀሳቡ የልቡ ሰመረ
 የሰላሙን ባለቤት የደስታዉን
 ኩራት ክብሩን ጋሻዉን መከታዉን ሰቶት አቻዉን
 ከእንግዲህ ብቸኝነት ቀረ
 የሀሳቧ የልቧ ሰመረ
 የሰላሟን ባለቤት የደስታዋን
 ኩራት ክብሯን ጋሻዋን መከታዋን
 ሰቷት አቻዋን
 ይትባረክ እንደ አብርሃም
 ይትባረክ እንደ አብርሃም
 እህ ዘላለም ዘላለም ዘላለም
 ዘላለም ይትባረክ እንደ አብርሃም
 ይትባረክ እንደ አብርሃም ይትባረክ እንደ አብርሃም
 እህ ዘላለም ዘላለም ዘላለም
 ዘላለም ይትባረክ እንደ አብርሃም
 ቃና ዘገሊላ እንደ አብርሃም
 ከሰርጉ ተገኝተን እንደ አብርሃም
 ድንቅ የፈፀምክ አምላክ እንደ አብርሃም
 ትዕንግርት አሳይተህ እንደ አብርሃም
 ዉሃዉን በታምር እንደ አብርሃም
 ወይን ያደረከዉ እንደ አብርሃም
 የሙሽሮቹንም እንደ አብርሃም
 ሰርጋቸዉን ባርከዉ እንደ አብርሃም
 እህ ዘላለም ዘላለም ዘላለም ዘላለም
 ይትባረክ እንደ አብርሃም
 ቅድስት ድንግል ማሪያም እንደ አብርሃም
 እሩዉሃ እመቤት እንደ አብርሃም
 በቃና ተገኝተሸ እንደ አብርሃም
 ከሰርገኞቹ ቤት እንደ አብርሃም
 የሚያዘዉን ሁሉ እንደ አብርሃም
 አድርጉ እንዳሻቻቸዉ እንደ አብርሃም
 ዛሬም ለሙሽሮች እንደ አብርሃም
 መንገዱን ምሪያቸዉ እንደ አብርሃም
 እህ ዘላለም ዘላለም ዘላለም ዘላለም
 ይትባረክ እንደ አብርሃም
 ይትባረክ እንደ አብርሃም
 ይትባረክ እንደ አብርሃም
 እህ ዘላለም ዘላለም ዘላለም ዘላለም
 ይትባረክ እንደ አብርሃም
 አንተዉ አገናኝተህ እንደ አብርሃም
 አስተዋዉቀሃቸዉ እንደ አብርሃም
 ለቅዱስ ጋብቻ እንደ አብርሃም
 እንዳበቃሀቸዉ እንደ አብርሃም
 እግዚአብሔር አምላክ ሆይ እንደ አብርሃም
 የፍቅር ባለቤት እንደ አብርሃም
 ይሙላ በረከትህ እንደ አብርሃም
 በሙሽሮቹ ቤት እንደ አብርሃም
 እህ ዘላለም ዘላለም ዘላለም ዘላለም
 ይትባረክ እንደ አብርሃም
 እህ ዘላለም ዘላለም ዘላለም ዘላለም
 ይትባረክ እንደ አብርሃም
 

Audio Features

Song Details

Duration
06:18
Key
9
Tempo
180 BPM

Share

More Songs by Tsegaye Eshetu

Similar Songs