Be-Gudde Ewotana
Lyrics
ጥርስሽን አይና እወደውና ዓይንሽን አይና አፈቅረውና በጉዴ እወጣለሁ በሕልሜ አወራና በጉዴ እንዳልወጣ በሕልሜ አወራና ጥርስሽን አይና አፈቅረውና ዓይንሽን አይና እወደውና በጉዴ እወጣለሁ በሕልሜ አወራና በጉዴ እንዳልወጣ በሕልሜ አወራና ♪ ተፈጥሮ ልጋሴን እንደምን ችሮሻል የወርቁን ማዕጠንት አርከፍክፎብሻል እማኝ በሌለበት በሕልሜ ትመጪና ጉድ እንዳይፈላብኝ ተኝቼ አወራና ዓይንሽማ ካድማስ ማዶ ሲያበራ ፍቅር ገበያው ደራ ጥርስሽማ በጨለማው ደመቀ ፈገግታሽ የጠለቀ ፀጉርሽማ ሀር መሳይ ጉንጉን አረገኝ ብክንክን ዳሌሽማ ሲተራመስ ሲቆጣ መጨነቅ ነው የኔ ዕጣ አወይ ሽንጧ አወይ ዳሌ በይ ደግፊኝ እንዳመሌ ኧረ ሙን ኧረ ሙን እኔም አልኩኝ ብክንክን ኧረ ሙን ኧረ ሙን ቆሜ ቀረሁ ሳይ ዓይኗን ቆሜ ቀረሁ ሳይ ጥርሷን ፈዝዤ አደርኩ ሳይ ዓይኗን ♪ ጥርስሽን አይና እወደውና ዓይንሽን አይና አፈቅረውና በጉዴ እወጣለሁ በሕልሜ አወራና በጉዴ እንዳልወጣ በሕልሜ አወራና ዓይንሽን አይና እወደውና ጥርስሽን አይና አፈቅረውና በጉዴ እወጣለሁ በሕልሜ አወራና በጉዴ እንዳልወጣ በሕልሜ አወራና ♪ ኩሩ ነች እያሉ ያሙሻል ሰዎቹ ሲያዩሽ ውለው ቢያድሩ መቼም አይሰለቹ ውበት እና ፀባይ ከተገጣጠመ እንዲህ ነው ካልቀረ ልብ እያደከመ ድምፅሽማ ዜመኛ የተለየ ወይ ዘንድሮ እኔን ያየ ሽንጥሽማ ዙሪያው እቅፍ አይሞላ ውበት ሚዛኑ አደላ ዳሌሽማ ሲተራመስ ሲቆጣ መጨነቅ ነው የኔ ዕጣ በእህል ውሃ መች ይኖራል ብለሽ አብሬሽ ልብነሽነሽ አቤት ውበት ኧረ ድንቅ እኔም አልኩኝ ፍልቅልቅ አወይ ገላ አወይ ሙን እስኪ አድርጊኝ ሽሙንሙን ኧረ ሙን ኧረ ሙን ቆሜ ቀረሁ ሳይ ጥርሷን ቆሜ ቀረሁ ሳይ ዓይኗን ፈዝዤ አደርኩ ሳይ ጥርሷን
Audio Features
Song Details
- Duration
- 05:44
- Key
- 2
- Tempo
- 173 BPM