Bèmèlkesh Aydèlèm

6 views

Lyrics

በመልክሽ አይደለም
 ዉበትሽን የማውቀው
 በዝናሽ አይደለም
 ስምሽን የማደንቀው
 በጨዋነትሽ ነዉ
 በእዉነተኛነትሽ
 ያንችን ትልቅነት
 እመቤትነትሽን
 በመልክሽ አይደለም
 ዉበትሽን የማውቀው
 በዝናሽ አይደለም
 ስምሽን የማደንቀው
 በአጨዋወትሽ ነዉ
 በእዉነተኛነትሽ
 ያንችን ትልቅነት
 እመቤትነትሽን
 በመልክሽ አይደለም
 ዉበትሽን የማውቀው
 በዝናሽ አይደለም
 ስምሽን የማደንቀው
 ፀገዬ የኔ እመቤት
 በአጨዋወትሽ ነው
 እመቤቴ በእውነተኛነትሽ
 ያንችን ትልቅነት
 እመቤትነትሽን
 በመልክሽ አይደለም
 ዉበትሽን የማውቀው
 በዝናሽ አይደለም
 ስምሽን የማደንቀው
 ፀገዬ እመቤቴ
 በአጨዋወትሽ ነው
 በእውነተኛነትሽ
 እመቤቴ ያንችን ትልቅነት
 እመቤትነትሽን
 ፀግዬ በሕይወት እያለሽ እመቤቴ ነበርሽ
 አሁንም ወደሰማይ ከሄድሽ በኋላ
 እመቤቴ ነሽ
 ከአራት ወር በኋላ ነሃሴ ፲፮ ፳፻፰
 ወደ ሰማይ ከሄድሽ ፴፪ ዓመት ሆኖሻል
 እመቤቴ ፀግዬ ይሄን ሁሉ ዓመት
 ፎቶግራፍሽን ይዤ ነው ምተኛው
 ይሄን ሁሉ ምናገርበት ሰው
 እንዴት ይወዳታል እንዲለኝ አደለም
 ግን ይሄን መደበቅ ስላልቻልኩ ነው
 ሁልጊዜ ቶሎ እንዲመሽ እፈልጋለሁ ቶሎ
 ሌላ ምክንያት የለውም
 ፎቶግራፍሸን አልጋዬ ላይ ነው ትቸው ስሜሽ የምወጣው
 ቶሎ በሚመሽበት ጊዜ እቅፍ አርጌው ፎቶግራፍሽን
 እተኛለሁ
 እውነቱን ለመናገር ልክ እንዳለሽ እንደድሮው
 የእመቤቴ እመቤት እመቤት እመቤት ነሽ ፀግዬ
 እና ባንቺ እኮራለሁ ከልብ እና አይዞሽ በቅርብ እንገናኛለን
 ክቡራትና ክቡራን ይህን ዘፈን ምናቀርበው
 በጣም እድለኞች ለሆናችሁ፣
 ፍቅረኞቻችሁ አብረው በሕይወት ላሉ፣
 እና ለታደላችሁ
 ይሄንን የእግዚአብሔር ስጦታ ተቀብላችሁ ፍቅረኞቻችሁን አንድ በአንድ በማግኘታችሁ
 ደስ ብሏችሁ እንድትኖሩ እና
 ለእንደኔ አይነት ፍቅረኞቻቸው ላለፉባቸው፣
 አብረው ላልሆኑ፣ ለሞቱባቸው፣ ለተለያዩ
 የተለያዩት ይቅርታ ተደራርገው እንደገና ፍቅራቸውን ለመመስረት የሚችሉበት ብዙ አይነት ምከንያቶች አሉ
 እና ደግሞ ከዚህ የበለጠ የሚያስደስት የለም
 ሌሎቻችን ፍቅረኞቻችን ያለፉብን ተፅናንተን
 ተፅናንተን ጸሎት በማረግ ሁልጊዜ ከአእምሮኣችን
 ሁልጊዜ በማሰብ ልክ እንዳሉ አርገን መውደድ
 እንችላለን
 እና በጥሞና ስለሰማችሁን በጣም እናመሰግናለን

Audio Features

Song Details

Duration
09:28
Key
10
Tempo
100 BPM

Share

More Songs by Girma Bèyènè

Albums by Girma Bèyènè

Similar Songs