7 Sebat

2 views

Lyrics

ሰባት 7 ፯ - አብዱ ኪያር
 ትላንት የማውቀውን ሁሉንም ቢያሳጣኝ
 ከፍቶኝ ተቀይሬ የሚያቀኝም ቢያጣኝ
 ፊቴ ተጨማዶ መልኬ ቢለወጥም
 ተደስቶ መሳቅ ጥርሴ ቢያቋርጥም
 ድህነትን በሞት መቸም አልለውጥም
 ሰባት ሰባት ጊዜ ብወድቅም
 ሰባት ሰባት ጊዜ ብወድቅም ሰባተኛ እነሳለሁ
 ከዜሮ መጀመርን አድጌበታለሁ
 ሰባት ሰባት ጊዜ ብወድቅም
 ሰባት ሰባት ጊዜ ብወድቅም ሰባተኛ እነሳለሁ
 ከዜሮ መጀመርን አድጌበታለሁ
 ትላንት የነበረኝ ዛሬ ባይኖረኝም
 ወዳጆቼ ጠፍተው ፍቅሬ ብትርቀኝም
 አይኔ ጥሩ ነገር ቢተውም ማየቱን
 እጄም ለቅንነት ቢያቆም መዘርጋቱን
 መቸም አላቆምም ተመስገን ማለቱን
 ሰባት ሰባት ጊዜ ብወድቅም
 ሰባት ሰባት ጊዜ ብወድቅም ሰባተኛ እነሳለሁ
 ከዜሮ መጀመርን አድጌበታለሁ
 ሰባት ሰባት ጊዜ ብወድቅም
 ሰባት ሰባት ጊዜ ብወድቅም ሰባተኛ እነሳለሁ
 ከዜሮ መጀመርን አድጌበታለሁ
 

Audio Features

Song Details

Duration
04:41
Key
10
Tempo
115 BPM

Share

More Songs by Abdu Kiar

Albums by Abdu Kiar

Similar Songs