Fiker Beamargna

2 views

Lyrics

ፍቅር በአማርኛ
 'ሀ' ብሎ ሃበሻ ፊደሉን ቆጠረ
 'ተ' ብሎ ተማሪ ቅኔን በረበረ
 ሰሙንም አገኘው ለምኖ እያደረ
 ወርቁን ግን ፍለጋ ስደትን ጀመረ
 ኣኣኣኣ
 ምርር አላት ኑሮ አስጠላት ስደቱ
 ሞልቶ አይሞላ ነገር ጧት ማታ መልፋቱ
 ስትከፋ እያየህ ኧረ ዝም አትበላት
 ወንዱ ያገሬ ልጅ ካላንተስ ማን አላት
 ለእንጀራ እንጂ ፈረንጂኛ
 ስንዋደድ እኛ ለኛ
 የሚያምርብን አገርኛ
 ፍቅር በአማርኛ
 ለእንጀራ እንጂ ፈረንጂኛ
 ስንዋደድ እኛ ለኛ
 የሚያምርብን አገርኛ
 ፍቅር በአማርኛ
 ምን ይዤ ነው ምመለሰው
 አወጣጤ ወርቁን ላፍሰው
 ትልቅ መስሎኝ ሳይ ከማዶ
 የስደት ሲሳይ ስቀርበው ባዶ
 ኣኣኣኣ
 እንደምን አድረሃል አይለው ጎረቤቱ
 ቢደሰት ቢከፋ እዛው ዘግቶ ቤቱን
 አንቺ ያበሻ ልጅ ጭንቀቱን እያየሽ
 ካንቺ ሌላ ለሱ ማን አለው ትያለሽ
 ለእንጀራ እንጂ ፈረንጂኛ
 ስንዋደድ እኛ ለኛ
 የሚያምርብን አገርኛ
 ፍቅር በአማርኛ
 ለእንጀራ እንጂ ፈረንጂኛ
 ስንዋደድ እኛ ለኛ
 የሚያምርብን አገርኛ
 ፍቅር በአማርኛ
 ምን ይዤ ነው ምመለሰው
 በዛ ይፈሳል በዚ ስይዘው
 ስደት ክፉ እምቢ ሲለኝ
 ካለ አገሬ ሰው እኔስ ማናለኝ
 እሱስ ማን አለው እሷስ ማን አላት
 እኔስ ማን አለኝ እምቢ ሲለኝ
 እኛስ ማን አለን ማን አለን እኛ
 አማርኛ
 

Audio Features

Song Details

Duration
04:20
Key
11
Tempo
100 BPM

Share

More Songs by Abdu Kiar

Albums by Abdu Kiar

Similar Songs