Gizie

6 views

Lyrics

ጊዜ ጌታ
 ሰላም ነሽ ወይ ጤና ድምጽሽ ጠፋ ምነው?
 ተስማማሽ ወይ ኑሮ አገሩስ እንዴት ነው?
 እኔ አልቻልኩበትም በጣም አቅቶኛል
 ዉብ አይንሽን እስካይ ጭንቅ ብሎኛል
 ጊዜ ጌታ ስትጥል ስታነሳ
 ጊዜ ጌታ ስትሰጥ ስትነሳ
 ጊዜ ጌታ አደራ አደራ አደራ
 ጊዜ ጌታ ጸሎቴን እንዳትረሳ
 አቤት አቤት ደስታ ያኔ የነበረው
 ምነው ተገናኝተን ዛሬም በደገምነው
 እንባ ይቅር እንባ አታልቅሽ የኔ እናት
 ዉብ አይንሽን ላዘን እሱ መች ፈጠራት
 እኔ አላማርርም ተለያየን ብዬ
 ሳይደግስ አይጣላም አይዞሽ እናትዬ
 ደሞስ አማርሬ እኔ ምን ላመጣ
 ለኔ ብሎ አይሮጥም ያው ነው ጊዜ ጌታ
 ጊዜ ጌታ ጊዜ ጌታ ስትጥል ስታነሳ
 ጊዜ ጌታ ጊዜ ጌታ ስትሰጥ ስትነሳ
 ጊዜ ጌታ ጊዜ ጌታ አደራ አደራ አደራ
 ጊዜ ጌታ ጊዜ ጌታ ጸሎቴን እንዳትረሳ
 በፍቅር በደስታ ስንቱን አሳልፈን
 አይመስለኝም ነበር ምንኖር ተለያይተን
 ሁሌ የማፈቅረው ሳቅ ጨዋታሽ ቀርቶ
 የኔ እናት ቁጣሽም ይታየኛል ጎልቶ
 እኔ አላማርርም ተለያየን ብዬ
 ሳይደግስ አይጣላም አይዞሽ እናትዬ
 ደሞስ አማርሬ እኔ ምን ላመጣ
 ለኔ ብሎ አይሮጥም ያው ነው ጊዜ ጌታ
 ጊዜ ጌታ ጊዜ ጌታ ስትጥል ስታነሳ
 ጊዜ ጌታ ጊዜ ጌታ ስትሰጥ ስትነሳ
 ጊዜ ጌታ ጊዜ ጌታ አደራ አደራ አደራ
 ጊዜ ጌታ ጊዜ ጌታ ጸሎቴን እንዳትረሳ
 

Audio Features

Song Details

Duration
05:06
Key
6
Tempo
180 BPM

Share

More Songs by Abdu Kiar

Albums by Abdu Kiar

Similar Songs