Yekedama Inatun

6 views

Lyrics

ቤት ያፈራዉን የአቅሟን ሰራርታ
 ትጠብቃለች ልጆቿን ጠርታ ልጆቿን ጠርታ
 ቤት ያፈራዉን የአቅሟን ሰራርታ
 ትጠብቃለች ልጆቿን ጠርታ ካሉበት ቦታ
 አንተ ፈጣሪ ጸሎቷን ስማ
 ስደት ልጆቿን ሁሌ እየቀማ
 ባሉበት ቦታ አሳካላቸው
 ሚስኪኗ ኢትዮጵያ በዓይኗ ትያቸው
 አንተ ፈጣሪ ጸሎቷን ስማ
 ስደት ልጆቿን ሁሌ እየቀማ
 ባሉበት ቦታ አሳካላቸው
 ሚስኪኗ ኢትዮጵያ በዓይኗ ትያቸው
 ያልገቡበት የለም ያልገቡበት የለም
 ያልገቡበት የለም አዬ ያልገቡበት የለም
 ሙቀትና ብርዱን ችለዉ በዚች ዓለም
 ይህቺ ቀን ታልፋለች እያሉ በማለም
 ስትጣሪ ያልመጡት ጠልተዉሽ አይደለም
 እናቱን 'ሚጠላ ከአንቺ አልተፈጠረም
 የከዳማ እናቱን እንጂ ሐበሻነቱን
 የከዳማ እናቱን እንጂ ሐበሻነቱን
 የከዳማ እናቱን እንጂ ሐበሻነቱን
 የከዳማ እናቱን እንጂ ሐበሻነቱን
 ምንም ቢቸግራት ምንም ቢቸግራት
 በማንም አልቀይር እናቴስ እናት ናት
 ደሞ ለእናትነት ደሞ ለእናትነት
 ማን ይወዳደራል እስቲ ከአዱ ገነት
 ቤት ያፈራዉን የአቅሟን ሰራርታ
 ትጠብቃለች ልጆቿን ጠርታ ልጆቿን ጠርታ
 ቤት ያፈራዉን የአቅሟን ሰራርታ
 ትጠብቃለች ልጆቿን ጠርታ ካሉበት ቦታ
 አንተ ፈጣሪ ጸሎቷን ስማ
 ስደት ልጆቿን ሁሌ እየቀማ
 ባሉበት ቦታ አሳካላቸው
 ሚስኪኗ ኢትዮጵያ በዓይኗ ትያቸው
 አንተ ፈጣሪ ጸሎቷን ስማ
 ስደት ልጆቿን ሁሌ እየቀማ
 ባሉበት ቦታ አሳካላቸው
 ሚስኪኗ ኢትዮጵያ በዓይኗ ትያቸው
 አቤት ብታያቸዉ አቤት ብታያቸው
 አቤት ብታያቸዉ እማማ አቤት ብታያቸው
 እህልና ውሃ ማርና ወተታቸው
 አርቴፊሻል ሆነ እንዳለ ኑሮአቸው
 ዘመናዊዉ ባርነት ስላስገደዳቸው
 ዜግነት ቀየሩ ካዱኝ አትበያቸው
 በወረቀት የሰዉ በደም የአንቺ ናቸው
 በወረቀት የሰዉ በደም የአንቺ ናቸው
 አሜሪካዊ ቢሉት ጋሼን አይቀይሩት
 አውሮፓዊም ቢሏት እታለም አይገርማት
 አረብ ሀገር ለፍታ ሚጡዬም ለእናቷ
 ምንም ምንም ቢሉኝ እኔንም አይቀይሩኝ
 ምንም ቢቸግራት ምንም ቢቸግራት
 በማንም አልቀይር እናቴስ እናት ናት
 ደሞ ለእናትነት ደሞ ለእናትነት
 ማን ይወዳደራል እስቲ ከአዱ ገነት
 ምንም ቢቸግራት ምንም ቢቸግራት
 በማንም አልቀይር እናቴስ እናት ናት
 ደሞ ለእናትነት ደሞ ለእናትነት
 ማን ይወዳደራል እስቲ ከአዱ ገነት
 ምንም ቢቸግራት ምንም ቢቸግራት
 በማንም አልቀይር እናቴስ እናት ናት
 ደሞ ለእናትነት ደሞ ለእናትነት
 ማን ይወዳደራል እስቲ ከአዱ ገነት
 

Audio Features

Song Details

Duration
06:38
Key
6
Tempo
120 BPM

Share

More Songs by Abdu Kiar

Albums by Abdu Kiar

Similar Songs