Yetm Yetm Linur

5 views

Lyrics

የመጀመርያ ቀን ገና አፌን ስፈታ
 እማማ የሚል ቃል ያኔ ካፌ ወጣ
 እማማ ያኔ ካፌ ወጣ
 እስከዛሬ ድረስ ቃሉን ሳስታውሰው
 እማማ ብቻ ነው የሚመላለሰው
 እማማ ነው የሚመላለሰው
 የትም የትም የትም ልኑር የትም አገር ልግባ
 በማንም የማይቀየር ልቤ ለብሷል ካባ
 ልቤ ልዩ ካባ ለብሶ ሁሉም ተገረሙ
 አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ነው ቀለሙ
 እኔ አገሬን አገሬ ምላት
 ልወድቅላት ነው ወይ ልሞትላት
 እኔ እማማን እማማ ምላት
 ልካድማት ነው ላገለግላት
 የትም የትም የትም ልኑር የትም አገር ልግባ
 በማንም የማይቀየር ልቤ ለብሷል ካባ
 ልቤ ልዩ ካባ ለብሶ ሁሉም ተገረሙ
 አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ነው ቀለሙ
 ሰው ባለም ላይ ሲኖር ሞትን ባይመኝም
 ለማማ እየለፋሁ ብሞት አይቆጨኝም
 ለማማ ብሞት አይቆጨኝም
 እንኳንስ ይቺ አለም ውሸት ያገነናት
 የገነትም ቁልፏ እማማ እግር ስር ናት
 ገነትም እማዬ እግር ስር ናት
 የትም የትም የትም ልኑር የትም አገር ልግባ
 በማንም የማይቀየር ልቤ ለብሱአል ካባ
 ልቤ ልዩ ካባ ለብሶ ሁሉም ተገረሙ
 አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ነው ቀለሙ
 እኔ አገሬን አገሬ ምላት
 ልወድቅላት ነው ወይ ልሞትላት
 እኔ እማማን እማማ ምላት
 ልካድማት ነው ላገለግላት
 የትም የትም የትም ልኑር የትም አገር ልግባ
 በማንም የማይቀየር ልቤ ለብሱአል ካባ
 ልቤ ልዩ ካባ ለብሶ ሁሉም ተገረሙ
 አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ነው ቀለሙ
 ሆሆሆ ሆሆሆ ሆሆሃሃ
 ሆሆሆ ሆሆሆ ሆሆሃሃ
 ሆሆሆ ሆሆሆ ሆሆሃሃ
 

Audio Features

Song Details

Duration
05:14
Key
11
Tempo
175 BPM

Share

More Songs by Abdu Kiar

Albums by Abdu Kiar

Similar Songs