Ylugneta Motowal

4 views

Lyrics

አብዱ ኪያር ይሉኝታ ሞቷል
 ፍቅርሽ እያሳየኝ ነው የማላውቀውን ደስታ
 ደሞም ያሰማኛል የስንቱን አሉባልታ
 እኔ ላንቺ ብለፋ ምናለ ምናለ
 አንድ ጊዜ እንጂ ሁለት ህይወት የለ
 አንድ ጊዜ እንጂ ሁለቴ ሞት የለ
 መዳከሜን አይቶ ወዳጅ ዘመድ ራቀ
 ተስፋ ቤቴ ጠፋ ልቤም ተጨነቀ
 ግን ጥሎ ማይጥለው ይመስገን ፈጣሪ
 የውስጤን አየና ሰጠኝ ጥሩ አፍቃሪ
 ማን ያቀናውን ማን ያዝበታል
 ላንቺ ነው ልቤ ለፍተሽበታል
 ሃቅ ልናገር ይሉኝታ ሞቷል
 ማን ያቀናውን ማን ያዝበታል
 ላንቺ ነው ልቤ ለፍተሽበታል
 ሃቅ ልናገር ይሉኝታ ሞቷል ዬ... ዬ... የስ... ይሉኝታ ሞቷል
 ፍቅርሽ እያሳየኝ ነው የማላውቀውን ደስታ
 ደሞም ያሰማኛል የስንቱን አሉባልታ
 እኔ ላንቺ ብለፋ ምናለ ምናለ
 አንድ ጊዜ እንጂ ሁለት ህይወት የለ
 አንድ ጊዜ እንጂ ሁለቴ ሞት የለ
 አይዞህ አይዞህ እያልሽ ይኸው ሁሉም አለፈ
 ለኔ ህይወት መሳካት ያንቺ ውበት ረገፈ
 ዛሬ ዘመድ ነኝ ባይ ያሻውን ቢያወራ
 ልቤ ላንቺ ብቻ ነው እንዳትሰጊ አደራ
 ምኖረው እኔ ሚፈርደው ሌላ
 ሚደክመው ልብሽ ሚያወራው ሌላ
 የታል ይሉኝታ ካሁን በኋላ
 ማን ያቀናውን ማን ያዝበታል
 ላንቺ ነው ልቤ ለፍተሽበታል
 ሃቅ ልናገር ይሉኝታ ሞቷል
 ማን ያቀናውን ማን ያዝበታል
 ላንቺ ነው ልቤ ለፍተሽበታል
 ሃቅ ልናገር ይሉኝታ ሞቷል ዬ... ዬ... የስ... ይሉኝታ ሞቷል
 

Audio Features

Song Details

Duration
05:14
Key
11
Tempo
120 BPM

Share

More Songs by Abdu Kiar

Albums by Abdu Kiar

Similar Songs