Etie Mietie

6 views

Lyrics

እንኳን አገኘሁሽ እንኳን ደና ቆየሽ
 እኔስ መስሎኝ ነበር ፈልጌ ማጣሽ
 እቴ የልጅነቴ የልጅነቴ እንዴት ነሽ
 እቴ የልጅነቴ የልጅነቴ እንዴት ነሽ
 ♪
 አይወስድሽም እያሉ ሲዘፍኑብሽ በይፋ
 በነገር ባሽሙራቸው እቴ አንገትሽ ሲደፋ
 ያ የጠበኩት ፍቅሬ ይኸው መጣ በያቸው
 ይዟት ይዟት በረረ እስቲ ሲሉ እንስማቸው
 የሄደ ሰው አይቀር እርቆ
 ይመለሳል ጊዜ ጠብቆ
 ከሩቅ ሀገር ስመጣ ቤትሽ
 አልተነካም ቃል እና እምነትሽ
 እቴ ሜቴ የሎሚ ሽታ ከዚህ በላይ ምን አለ ደስታ
 እቴ ሜቴ የሎሚ ሽታ ከዚህ በላይ ምን አለ ደስታ
 ♪
 እንኳን አገኘሁሽ እንኳን ደና ቆየሽ
 እኔስ መስሎኝ ነበር ፈልጌ ማጣሽ
 እቴ የልጅነቴ የልጅነቴ እንዴት ነሽ
 እቴ የልጅነቴ የልጅነቴ እንዴት ነሽ
 ♪
 እርሳት ይሉኝ ነበረ የሩቅ ሰው በማፍቀሬ
 ከንቱ ነበር ለነሱ ቃልኪዳኔን ማክበሬ
 ዛሬ ተገናኝተናል የምስራች ይነገር
 አምሯል ሸገኑ ብሎ አዎ እስቲ ይሸኘን ሀገር
 የሄደ ሰው አይቀር እርቆ
 ይመለሳል ጊዜ ጠብቆ
 ከሩቅ ሀገር ስመጣ ቤትሽ
 አልተነካም ቃል እና እምነትሽ
 እቴ ሜቴ የሎሚ ሽታ ከዚህ በላይ ምን አለ ደስታ
 እቴ ሜቴ የሎሚ ሽታ ከዚህ በላይ ምን አለ ደስታ
 ከቤቴ በላይ ፍቅር ሰፍሮ ፍቅር ሰፍሮ
 ትዝታው መጣ ይኸው በሮ ይኸው በሮ
 እኔን ሲያበረኝ ሲያከንፈኝ ሲያከንፈኝ
 ከወጣሁበት አመጣኝ አመጣኝ
 ከመጣውማ ወደ ቤቴ ወደ ቤቴ
 አንቺን ካገኘው እመቤቴን እመቤቴን
 የኔ እመቤት አትለይኝ
 እስከ ዘላለም ያንቺው ነኝ ያንቺው ነኝ
 ♪
 የሄደ ሰው አይቀር እርቆ
 ይመለሳል ጊዜ ጠብቆ
 ከሩቅ ሀገር ስመጣ ቤትሽ
 አልተነካም ቃል እና እምነትሽ
 እቴ ሜቴ የሎሚ ሽታ ከዚህ በላይ ምን አለ ደስታ
 እቴ ሜቴ የሎሚ ሽታ ከዚህ በላይ ምን አለ ደስታ
 

Audio Features

Song Details

Duration
06:13
Key
1
Tempo
105 BPM

Share

More Songs by Abdu Kiar

Albums by Abdu Kiar

Similar Songs